CURRENT

ለውጭ አገር የስራ ስምሪት ያለ በቂ ዝግጅት መሄድ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ተናገሩ

By Admin

March 09, 2017

ለውጭ አገር የስራ ስምሪት ያለ በቂ ዝግጅት መሄድ እንደማይቻል ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ተናገሩ ከገጠር የመጡ ምንም የማያውቁ ሴት ልጆች ወደ ውጭ የሚሄዱብት ሁኔታ ተፈጥሯል፡፡ ይህ ደግሞ በአገራችን የፈጠረው ችግር ከፍተኛ መሆኑን ሁሉም የሚያውቀው ነው ብለዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ የሚኬድባቸው አገሮችን በማሳመን ስምምነት ተፈራርመናል፡፡ ይህን ተፈጻሚ ለማድረግ ደግሞ ትንሽም ቢሆን ቋንቋ ማወቅና መለስተኛ ክህሎት ሊኖር ይገባል፡፡ ከአሁን በኋላ ስምንተኛ ያልጨረሰ ማንም ቢሆን በውጭ አገር ስምሪት ሊሰማራ አይችልም፡፡ ክልሎች ወጣቶች በቅተው ለውጭ አገር ስምሪት እንዲሄዱ ሥልጠና መስጠት ጀምረዋል፡፡ መንግስትም ይህ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ድጋፍ ያደርጋል ብለዋል፡፡፡