አይነፋም፤ የልብ አያደርስም

አይነፋም፤ የልብ አያደርስም

አይነፋም፤ የልብ አያደርስም ስሜነህ ሰሞኑን በከተማችን አዲስ አበባ ነዋሪዎች፣ በተለይም በወጣቱ ዘንድ “አይነፋም” የሚል  ወቅት አፈራሽ ቃል/ምላሽ መስማት ከመለመድም አልፎ የበርካቶች መግባቢያ በመሆን ላይ ይገኛል። “አይነፋም” የሚነገረው፣ የሚሰማው ጉዳይ ከሚጠበቀው ውጤት ጋር አልሰምር፤ አልጥም  ሲል የሚሰነዘር የቅሬታ ቃል/የሚሰጥ ምላሽ በመሆኑ እኔም እዚህ ልጠቀምበት ፈቀድሁ፤ አይነፋም። መንግስት ጉዳዩን አንድ ብሎ ካሳወቀበት ጊዜ ጀምሮ የጸረ ኪራይ ሰብሳቢነት ዘመቻው ምህዳሩን አስፍቶ፤ ምንጠራውን አጠናክሮ ቀጥሏል። ስልቱን የቀየረው ይህ አገር አቀፍ ዘመቻ በሃሰተኛ የትምህርት ማስረጃ (fake degree) ባለቤቶችም ጡንቻውን በማሰረፍ…

Read More

ለተሳለጠ የወጪ-ገቢ ንግድ ሲባል፤ የሎጀስቲክስ እና የጉሙሩክ አሰራር ስርአታችንን ይፈተሽ

ለተሳለጠ የወጪ-ገቢ ንግድ ሲባል፤ የሎጀስቲክስ እና የጉሙሩክ  አሰራር ስርአታችንን ይፈተሽ

ለተሳለጠ የወጪ-ገቢ ንግድ ሲባል፤ የሎጀስቲክስ እና የጉሙሩክ አሰራር ስርአታችንን ይፈተሽ ስሜነህ ለአገሪቱ የተፋጠነ ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ዕድገት የትራንስፖርት አገልግሎት የበለጠ ተወዳዳሪ፤ ደህንነቱ የተጠበቀና ብቃት ያለው ሆኖ እንዲራመድ ክትትል ስለሚያስፈልገው፤ የትራንስፖርት ዘርፉ አደረጃጀት የመንግሥት ፖሊሲን በአግባቡ ለመተግበር አመቺ ሁኔታ በሚፈጥር መልኩ እንደገና መዋቀር ስለሚገባው፤ ትራንስፖርትን አስመልክቶ የፌዴራልና የክልል አስፈጻሚ አካላት የተሰጣቸውን ሥልጣንና ተግባር በማያሻማ ሁኔታ ማስቀመጥ አስፈላጊ በመሆኑ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ ፶፭/፩/ መሠረት የትራንስፖርት ዘርፉን ለመቆጣጠር የሚያስችል አዋጅ (አዋጅ ቁጥር ፬፻፷፰/፲፱፻፺፯) መውጣቱ ይታወቃል፡፡ በዚሁ…

Read More

ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንድና ብቸኛው አማራጭ ነው!

ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ አንድና ብቸኛው አማራጭ ነው! ወንድይራድ ኃብተየስ በአገራችን ድጋፍንም ሆነ ተቃውሞን ሰላማዊ በሆነ መንገድ መግለጽ  ህገመንግስታዊ መብት ነው። በሰላማዊ መንገድ የሚካሄዱ ድጋፎችም  ይሁኑ ተቋውሞዎች  ክፋት የላቸውም። ህገመንግስታዊ መሰረትም ዋስትናም አላቸው።  ልዩነትን በሰላማዊ መንገድ በማራመድ የሃሳብ ብዘሃነትን ማሳየት የዴሞክራሲ አንዱ መገለጫ  ነው። በኢትዮጵያ በርካታ ልዩነቶች ይስተዋላሉ። ለአብናት የሃሳብ፣ የሃይማኖት፣ የብሄር፣ የባህል፣ ወዘተ። ኢትዮጵያን እንደአገር እናስቀጥላት የምንል ከሆነ ልዩነታችንን የሚያስተናግድ  ስርዓት  መከተል የግድ ይላል። ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን መተግበር  ለኢትዮጵያ አንድና  ብቸኛ  አማራጭ ነው።  በርካታ ፖለቲከኞች…

Read More

ለአርሶ  እና አርብቶ አደር ህይወት መለወጥ

ለአርሶ  እና አርብቶ አደር ህይወት መለወጥ አባ መላኩ   ኢትዮጵያ ልማትን ማረጋገጥ የህልውና ጉዳይ ነው በሚል መረባረብ ከጀመረች ሀያ አምስት ዓመታት አልፈዋል። ይህንን እውን ለማድረግ ደግሞ ዘርፈ ብዙ የልማት ግንባታ  እየተከናወነ ይገኛል። በአገሪቱ ፍትሃዊ ልማትን እውን ለማድረግና በተለይም ባለፉት ሥርዓታት ትኩረት ተነፍገው የነበሩ አርሶና አርብቶ አደሮች ከዚህ ልማት ተጠቃሚ ይሆኑ ዘንድ የግብርና ልማትን ማዕከል ያደረገ የልማት ስትራቴጂ ተነድፎ እየተሰራበት ይገኛል። አርብቶና አርሶ አደሩ ተዘፍቀውበት ከነበረው የከፋ ድህነት ተላቀው የተሻሻለ ህይወት እንዲኖሩ ለማስቻል ቀላል የማይባል ለውጥ…

Read More

የገዘፈው ግድብ !!

            የገዘፈው ግድብ !!                                         ይነበብ ይግለጡ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ በታላቅ ሀገራዊ ፍቅር ሥራው ቀን ከለሊት ቀጥሏል። በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ ግዙፍና አይነተኛ ለውጥ የሚያስገኝ ብዎቹን ብሔራዊ ሕልሞቻችንን ለማሳካት ታላቅ አቅም የሚፈጥር ነው። የሀገራችንን የውሀ ማማነት ከቃላት ባለፈ ሕይወት ባለውና በሚታይ ደረጃ ለአፍሪካም ለአለምም በተጨባጭ ያረጋግጣል፡፡ ከመላው አፍሪካ  ግዙፉና ቀዳሚው በአለም ደግሞ በትልቅነቱ በሰባተኛ ደረጃ የሚገኝ ነው የሚሆነው፡፡ የግድቡ ግንባታ ያለማንም የውጭ እርዳታና ድጋፍ በኢትዮጵያ ህዝብና መንግስት ገንዘብ ተጀምሮ አሁን ያለበት የ60 በመቶ ደረጃ ላይ መድረሱ…

Read More

የፀረ ሙስና ትግሉ!

የፀረ ሙስና ትግሉ!

የፀረ ሙስና ትግሉ!                                            ይነበብ ይግለጡ በሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት ላይ የተጀመረው ትግል ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡ መቀጠል ያለበት የሕዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ብቻ ሳይሆን ሙስናና ኪራይ ሰብሳቢነት መንግስታዊ ተቋማትን እያሽመደመደ ያለ የከፋ ችግር ከመሆኑም በላይ መልካም አስተዳደርና የፍትሕን መከበር የሚደፍቅ የዜጎችን መብት የሚጥስና የሚደፍር የመንግስትና የሕዝብን ሀብት በመዝረፍ ላይ ያነጣጠረ ለዚህም የሚሰራ በመሆኑ ነው፡፡ ሙሰኞችና ኪራይ ሰብሳቢዎች በመንግስትና በሕዝብ የተሰጣቸውን አደራ በመተላለፍ ብልሹ አሰራር እንዲሰፍን ሕዝብ ምሬት ውስጥ እንዲገባ አይነተኛ ሚና በመጫወት በመንግስትና በሕዝብ መካከል ከፍተኛ አለመተማመን…

Read More

የወጪ ንግዱ ፈተናዎችና ተስፋዎች

የወጪ ንግዱ ፈተናዎችና ተስፋዎች

የወጪ ንግዱ ፈተናዎችና ተስፋዎች ብ. ነጋሽ የወጪ ንግድ በአንድ ሃገር ኢኪኖሚያዊ እድገት ውስጥ ወሳኝ ድርሻ አለው። በተለይ ሁሉንም ፍላጎታቸውን – ምርትና አገልግሎት በራሳቸው አቅም መሸፈን ለማይችሉት በማደግ ላይ ያሉ ሃገራት የወጪ ንግድ የማደግ ያለማደግ፤ የመልማት ያልመልማት ጥያቄ ነው። ይህ ብቻ ሳይሆን የሃገር የህልውና ጉዳይም ነው። ሁሉንም ፍላጎታቸውን በራሳቸው አቅም ማሟላት የማይችሉ ታዳጊ ሃገራት በሃገራቸው ውስጥ የማያመርቱትን የሚያሟሉት በገቢ ነግድ ነው። የገቢ ንግድ ደግሞ የውጭ ምንዛሪ ይጠይቃል። የውጭ ምንዛሪው ቱሪዝምን ከመሳሰሉ የአገልግሎት ዘርፎችና ከቀጥታ የውጭ ኢንቨስትመንት…

Read More

የ“ዴሞክራሲያውያኑ” ኢ-ዴሞክራሲያዊ ጎዳና

የ“ዴሞክራሲያውያኑ” ኢ-ዴሞክራሲያዊ ጎዳና

የ“ዴሞክራሲያውያኑ” ኢ-ዴሞክራሲያዊ ጎዳና ኢብሳ ነመራ አሜሪካ አሁን ባለንበት ዘመን የሰው ልጆችን እኩልነት ለመቀበል የቸገራት ሃገር ነች። በአሜሪካ በርካታ ጥቁሮች ቢኖሩም እኩልነታቸውን መቀበል ለነጮቹ ጭንቅ የሆነባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያሳዩ አስረጂዎች አሉ። እርግጥ የአሜሪካ ታሪክም ይህን የሚያሳይ ነው። የአሜሪካ መስራች አባት የሚባለውና የአሜሪካን የነጻነት መግለጫ ሰነድ (Declaration of Independence) ያዘጋጀው ቶማስ ጀፈርሰን፣ ይህን ድንቅ የሰውን ልጆች እኩልነትና የሰብአዊ መብት መከበር የሚገልጽ ሰነድ ሲያዘጋጅ በቤቱ እንደእንስሳ በንብረትነት የያዛቸው ጥቁር ባሪያዎች ነበሩት። ስለሰው ልጅ ነጻነት ያን ያህል ሲያስብና ሲጽፍ…

Read More

በመሞት ላይ ያለ አመለካካት አራማጆች ህልም

በመሞት ላይ ያለ አመለካካት አራማጆች ህልም

በመሞት ላይ ያለ አመለካካት አራማጆች ህልም ኢብሳ ነመራ እያንዳንዱ ዘመን የሶስት ትውልድ አመለካከቶች ህልውናቸውን ለማስጠበቅ የሚፋለሙበት መድረክ ነው። እነዚህም አሁን ያለው ገዢ አመለካካት፣ ያለፈውና በመሞት ላይ የሚገኘው አመለካካት እንዲሁም ልወለድ የሚለው የመጪው ዘመን አመለካከቶች የሚፋለሙበት መድረክ ነው። የማህበረሰብ እድገት በተለየ አጋጣሚ ለተወሰነ ጊዜ ሊገታ ወይም ሊጓተት የሚችልበት አጋጣሚ መኖሩ ባይካድም፣ ዋናው አቅጣጫው ግን በጊዜ ጎዳና ላይ አሮጌውን እየለወጠ ወደፊት የሚዘልቅ ነው። የማህበረሰብ እድገት ታሪክ ወደኋላ አይመለስም፤ ወይም አይቀለበስም። በዚህ ጉዞ ውስጥ አሮጌው በቀላሉ አይሞትም፣ መጪውም…

Read More

ህዝብ ያልተቀበለውን ጫካ አይሸሽገውም

ህዝብ ያልተቀበለውን ጫካ አይሸሽገውም

ህዝብ ያልተቀበለውን ጫካ አይሸሽገውም ብ. ነጋሽ ኢትዮጵያ ከ1980ዎቹ ማገባደጃ ጀምሮ በተደጋጋሚ የሽብር ጥቃት ሰለባ ሆና ቆይታለች። የሽብር ጥቃቶቹ ንጹሃን ዜጎችን ዒላማ ያደረጉ ነበሩ። ጥቃቶቹ የተሰነዘሩት ሰላማዊ ዜጎች የሚሰበሰቡባቸው ሆቴሎች፣ ምግብ ቤቶች፣ የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ጎዳናዎች ወዘተ ነበሩ። እስከ 2000 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ብቻ በመቶ የሚቆጠሩ ንጹሃን ኢትዮጵያውያን በሽብር ድርጊት ህይወታቸውን አጥተዋል። በመቶዎች የሚቆጠሩ ቋሚ የአካል ጉዳት አደጋ ደርሶባቸዋል። በሽብር ጥቃቶቹ፣ ህጻናት ያለአሳዳጊና ተንከባካቢ ወላጅ ቀርተዋል። አዛውንት ጧሪ አጥተዋል። ሰርተው ማደርና ሌሎችን መደገፍ…

Read More
1 2 3 67