ጃንሆይ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም እኮ አሟቷል

ጃንሆይ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም እኮ አሟቷል

በኢትዮጵያ አቆጣጠር 1960 ዎቹ አካባቢ ኢትዮጵያ አገራችን በብዙ ችግሮች በተወጠረችበት ወቅት ጃንሆይ ከልጅነታቸው ጀምሮ አብሮ አደጋቸው ከነበሩት ከራስ እምሩ ኃይለስላሴ ጋር በጃንሆይ ታላቁ ቤተመንግስት አብረው ተቀምጠው ሳለ የጃንሆይ ፊት፣ መልክ፣ አኳኋን አላማራቸውምና “ጃንሆይ ምን ሆነዋል በሰላም ነው? ፊትዎ ጠቁሯል ” አሏቸው። ጃንሆይም ” ጤንነት አይሰማንም አሞናል።” ሲሏቸውራስ እምሩ ኃይለስላሴም እንቅልፍ የነሳቸው ነገር የጃንሆይ ህመም ሳይሆን የአገራቸው የየዕለቱ ሁኔታ ነበርና ” ጃንሆይ እርስዎ ብቻ ሳይሆኑ ኢትዮጵያም እኮ አሟቷል።” ሲሉ ያገሪቷን ችግር ሕመም በጥበብ ነገሯቸው። ይባላል። አዎን…

Read More

በኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅራቢያ የደረቅ ወደቦች ግንባታ ሊካሄድ ነው

በኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅራቢያ የደረቅ ወደቦች ግንባታ ሊካሄድ ነው

ኢንዱስትሪ የሚመርቱ ምርቶችን በፍጥነት ወደ ውጪ ለመላክ እንዲቻል በኢንዱስትሪ ፓርኮች አቅራቢያ የደረቅ ወደቦች ግንባታ ሥራና የማስፋፋት ተግባር እንደሚያከናውን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ገለጸ። የድርጅቱ ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ገብረሕይወት እንደተናገሩት፥ አሁን ያሉትን ሰባት የደረቅ ወደቦች ከማስፋፋት ጎን ለጎን በኢንዱስትሪ ፓርኮች አካባቢም ደረቅ ወደቦች ይገነባሉ። እንደ አቶ ደሳለኝ ገለጻ በሃዋሳ ኢንዱስትሪ ፓርክ አቅራቢያ የደረቅ ወደብ ለመገንባት ዝግጅት እየተደረገ ሲሆን፥ በአማራ ክልል በወረታ ከተማም ሌላ የደረቅ ወደብ ለመገንባት የጥናት ሥራ እየተካሄደ ይገኛል። የደረቅ ወደቦች…

Read More

በአዲስ አበባ ቆሼ አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ ተደርምሶ እስካሁን የ46 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ ቆሼ አካባቢ በደረሰ የቆሻሻ ተደርምሶ እስካሁን የ46 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የተከመረ ቆሻሻ ተደርምሶ እስካሁን የ46 ሰዎች ህይወት አለፈ። ማምሻውን የአዲስ አበባ ከንቲባ ድሪባ ኩማ በሰጡት መግለጫ የሟቾቹ ቁጥር ወደ 46 ከፍ ብሏል። ከሟቾቹ ውስጥ 32 ሴቶች ሲሆኑ ቀሪዎቹ ደግሞ ወንዶች መሆናቸውንም ከንቲባው ገልጸዋል። አሁን ላይ አደጋውን የመቀነስ እና ህይዎት የማዳን ስራው እንደቀጠለ ነው ብለዋል። ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስም በአካባቢው የሚገኙትን ነዋሪዎች ራቅ ወዳለ ቦታ የማስፈር ስራ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል። ጉዳቱ ለደረሰባቸው ነዋሪዎችም የሰብዓዊና የተለያዩ ድጋፎች እየተደረገ ነው ያሉት ከንቲባው፥ ከተማ አስተዳደሩ ኮሚቴዎችን በማቋቋም ህይዎት የማዳኑንና የተጎዱትን የማቋቋም ስራ ከተለያዩ አካላት ጋር በመተባበር እየሰራ መሆኑንም ነው የተናገሩት። በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ተከምሮ የነበረው ቆሻሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው በሚገኙ ቤቶች ላይ ተደርምሶ ጉዳት አድርሷል። አደጋው ከሟቾች በተጨማሪም በርካታ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት አድርሷል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአለርት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

Read More

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ሀብት ያፈሩ አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች ሽልማት ተበረከተላቸው

ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ተጠቅመው ሀብት ያፈሩ አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች ሽልማት ተበረከተላቸው

በግብርና ዘርፍ ተሰማርተው ሃብት በማፍራት ወደ ኢንቨስትመንት የተሸጋገሩ ከ550 በላይ አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች ተሸለሙ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በአዳማ ከተማ በተከበረው፥ ስምንተኛው ሀገር አቀፍ የአርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች በዓል ተገኝተው ለሞዴል አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች ሽልማት ሰጥተዋል። ሞዴል አርሶ እና ከፊል አርብቶ አደሮች በግብርናው ዘርፍ ያገኙትን ልምድና እውቀት በተመሳሳይ ዘርፍ ለተሰማሩ እንዲያካፍሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ጠይቀዋል። አርሶና ከፊል አርብቶ አደሮች በግብርና ዘርፍ ባስመዘገቡት የላቀ አፈጻጸም ከቦንድ ጀምሮ እስከ ዘመናዊ ትራክተር…

Read More

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል

በአዲስ አበባ “ቆሼ” በሚባለው አካባቢ የቆሻሻ ክምር ተደርምሶ እስካሁን የ15 ሰዎች ህይወት አልፏል በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ስሙ ቆሼ ተብሎ በሚራው አካባቢ የቆሻሻ ክምር የመደርመስ አደጋ የተከሰተው ትላንት ምሽት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ገደማ ነበር፡፡ አደጋው በመኖሪያ ቤቶች ላይ የደረሰ በመሆኑ ለሰው ህይወትና ንበረት መጥፋት ምክንያት ሆኗል፡፡ ከአደጋው የተረፉ ነዋሪዎች እንደተናገሩት ሙሉ ንብረቶቻቸውና የሰው ህይወት ጉዳትና መጥፋት እንደገጠማቸው ተናግረዋል፡፡ የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ ድሪባ ኩማ አደጋው በደረሰበት ቦታ ተገኝተው እንዳሉት በአደጋው ምክንያት እስካሁን…

Read More

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀምራል

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ይጀምራል

የአማራ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤውን ነገ ማካሄድ ይጀምራል። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ ለአራት ቀናት በሚቆየው ጉባኤ፥ የበጀት አመቱ ስድስት ወራት የክልሉ የስራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ይደረግበታል። የአስፈጻሚ አካላት የተቃለለ የልማትና መልካም አስተዳደር እቅድ፣ የክልሉ የዳኝነት አካላት አፈጻጸም እቅድና የዋናው ኦዲተር መስሪያ ቤት የክዋኔ ኦዲት አፈጻጸም ሪፖርቶችም ቀርበው ይገመገማሉ። የምክር ቤቱ አፈጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ፥ ምክር ቤቱ በየዘርፉ የተፈጸሙ ተግባራትን የሚገመግም ቋሚ ኮሚቴ አቋቁሞ ክትትል ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል። አፈጻጸሙ ቀርቦም…

Read More

ከአዲስ አበባ ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

ከአዲስ አበባ ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ተጀመረ

ከአዲስ አበባ ሱዳን ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ዛሬ ተጀምሯል። አገልግሎቱ በሙከራ ደረጃ የተጀመረ ሲሆን፥ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች ግንኙነት ከማጎልበት አኳያ ከፍተኛ ፋይዳ ያለው መሆኑን፥ የትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል። በባለስልጣኑ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ በላቸው ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንዳሉት፥ የአገልግሎቱ መጀመር በካርቱም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችና በመካካለኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ የሁለቱም ሀገራት ዜጎች አማራጭ የመገናኛ ዘዴ ይሆናል። ለኢንቨስትመንትና ቱሪዝም እድገት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ የጎላ መሆኑንም ዳይሬክተሩ ተናግረዋል። አገልግሎቱን ለማስጀመርም ከኢትዮጵያ በኩል አባይ፣ ኢትዮ ባስ፣…

Read More

ዕድሜ የማይወስነው የኩላሊት ሕመም

ዕድሜ የማይወስነው የኩላሊት ሕመም

ሐሙስ የካቲት 30 ቀን 2009 ዓ.ም. ጠዋት ብሔራዊ ቲያትር መግቢያ በር ላይ ‹‹የዓለም የኩላሊት ቀን›› የሚል ጽሑፍ ያለበትና የሁለት ኩላሊቶች ምስል የታከለበት ባነር ተለጥፏል፡፡ ወደ ውስጥ ዘለቅ ሲባል ደግሞ ከወትሮው ለየት ባለ መልኩ ብዙ ሰዎች በሁለት ረድፍ ተሰልፈዋል፡፡ ከሰልፈኞቹም መካከል ግማሹ ይመዘገባል፣ ሌላው ይመዘናል፣ እኩሉ ደግሞ  የደም ግፊቱን ይለካል፡፡ ከተለያዩ ሕክምና ተቋማት የተውጣጡ ባለሙያዎችም ታዳሚውን በማስተናገድ ሥራ ተወጥረው ይስተዋላሉ፡፡የኩላሊት በሽታን ለማወቅ የሚያስችል ነፃ ምርመራ እየተካሄደም ነበር፡፡ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሕፃናትና የሕፃናት ኩላሊት  ሕክምና ስፔሻሊስት፣ ረዳት…

Read More

በኦሮሚያ ክልል 950 ሺ የሚደርሱ ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ የተለያዩ የሥራ መስኮች ለማሠማራት መታቀዱን

በኦሮሚያ ክልል 950 ሺ የሚደርሱ ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ የተለያዩ  የሥራ መስኮች ለማሠማራት መታቀዱን

በዘንድሮ የበጀት ዓመት በኦሮሚያ ክልል 950 ሺ የሚደርሱ ሥራ አጥ ወጣቶችን ወደ የተለያዩ  የሥራ መስኮች ለማሠማራት መታቀዱን የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ አስታወቀ ።የቢሮው ምክትል ኃላፊ አቶ ባህሩ ተክሌ ለዋልታ እንደገለጹት በኦሮሚያ ክልል የሥራ አጥ ወጣቶችን ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን ለመፍታት በክልሉ በሥራ አጥነት ከተለዩት አጠቃላይ 1 ሚሊዮን 200 ሺ ወጣቶች መካከል 950  ሺ የሚሆኑትን ወጣቶች በዘንድሮ ዓመት  በተለያዩ የሥራ መስኮች ለማሠማራት ታቅዷል ።የፌደራል መንግሥት ከመደበው አጠቃላይ 10 ቢሊዮን ብር የተዘዋዋሪ ፈንድ ውስጥ 3ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር…

Read More

ግዙፍ የአሜሪካና የቻይና ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

ግዙፍ የአሜሪካና የቻይና ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ እየገቡ ነው

ግዙፍ የሆኑ የአሜሪካና የቻይና ኩባንያዎች በኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ በመምጣት ላይ መሆናቸውን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የኢንቨስትመንት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ ተካ ገብረኢየሱስ የካቲት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት መግለጫ፣ ጂያንግሱ ሰንሻይን ግሩፕ የተሰኘ ግዙፍ የቻይና ኩባንያ በኢትዮጵያ 945 ሚሊዮን ዶላር ኢንቨስት ለማድረግ መወሰኑን ገልጸዋል፡፡ ጂያንግሱ ታዋቂ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት አምራች ኩባንያ መሆኑንና በኢትዮጵያ በአዳማ ከተማ ግዙፍ የሱፍ ጨርቅ ማምረቻ ለማቋቋም የሚያስችለውን ስምምነት የኩባንያው ፕሬዚዳንት አዲስ አበባ በመምጣት መፈረማቸውን አቶ…

Read More
1 2