አቶ ዛዲግ አብርሀ ከሰላም ራዲዮ ጋር

አቶ ዛዲግ አብርሀ ከሰላም ራዲዮ ጋር

ከመንግስት ኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ከአቶ ዛዲግ አብረሃ ጋር በአንዳንድ በሃገሪቱ አካባቢዎች የተከሰተውን ድርቅ አስመልክቶ በመንግስት በኩል እየተደረገ ያለውን እንቅስቃሴ በተመለከተ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ያስገኘውን ለውጥ አስመልክቶ ውይይት አድርጓል። እንድትከታተሉት ጋበዝናችሁ !!!

Read More

በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻዕብያ ወታደሮች መካከል ውግያ ተቀሰቀሰ።

በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻዕብያ ወታደሮች መካከል ውግያ ተቀሰቀሰ።

በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻዕብያ ወታደሮች መካከል ውግያ ተቀሰቀሰ። ውግያው የተቀሰቀሰው መረብ-ለኸ/ራማ/ ወረዳ ተሻግሮ ክሳድ ዒቃ በሚባል ስፍራ በኤርትራ ነፃ አውጪ /ዴምሐኤ/ ወታደሮችና በሻብያ ወታደሮች መካከል ሲሆን በውግያው ኮነሬል ኣባዲ ገብረ መዓሾ/ወዲ ገብሩ/ የተባለ የጦር መሪን ጨምሮ 58 የሻዕብያ ወታደሮች መገደላቸው ታውቋል። ውግያው እስከ አሁን መቀጠሉንም የመረብ ለኸ ወረዳ ፀጥታ ፅ\ቤት አስታውቋል።

Read More

‹‹ፖለቲካ-ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ››

‹‹ፖለቲካ-ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ››

‹‹ፖለቲካ-ኢኮኖሚና የኢትዮጵያ ህዳሴ›› በሚል በጓድ አለምነው መኮነን ተፅፎ ሰሞኑን በክልል ደረጃ የተመረቀው መፅሀፍ የት ማግኘት እንደሚቻል በርካታ የገፃችን ደንበኞች በገፃችን ጥያቄ ጠይቃችኋል፡፡በዚህም መሰረት በባህርዳር ከተማ መፅሃፏ ወደ ገበያ የገባች ሲሆን መፅሀፉን ለማግኘት ደግሞ በ 0911593015 በመደወል መፅሀፉን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ በቀጣይም የሌሎች ከተሞች የመፅሀፍ ሽያጭ ወኪሎችን የምናሳውቅ ይሆናል፡፡

Read More

የወሰን ማካለል ጉዳይ የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም – ጠ/ሚ ኃይለማርያም

የወሰን ማካለል ጉዳይ የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም – ጠ/ሚ ኃይለማርያም

የወሰን ማካለል ጉዳይ “በምንም ዓይነት የግጭት መንስኤ ሊሆን አይችልም” አሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ። ሴቶችና ህጻናት በወሰን አካባቢ በሚነሱ ግጭቶች ምክንያት የሚደርስባቸውን ጉዳት ለመቀነስ እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል። ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን (ማርች 8) አዲስ አበባና ድሬደዋ አስተዳደርን ጨምሮ ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ሴቶች ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋር ውይይት በማድረግ አክብረዋል። በዚሁ ወቅት የሁሉም ክልል ተወካይ ሴቶች ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ያላቸውን ጥያቄ አቅርበው ማብራርያ ተሰጥቶባቸዋል። በወሰን አካባቢ በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያት ሴቶችና ህጻናት ዋነኛ ተጎጂ በመሆናቸው መንግስት ችግሩን ለመፍታት ያለውን…

Read More

ደቡብ አፍሪካ በፕሬዚዳንት አልበሽር ምክንያት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች

ደቡብ አፍሪካ በፕሬዚዳንት አልበሽር ምክንያት በአለም አቀፉ የወንጀለኞች

ደቡብ አፍሪካ የሱዳኑን ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽርን አሳልፋ ባለመስጠቷ ምክንያት የአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ልትቀርብ ነው። በአለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት የእስር ማዘዣ የተቆረጠባቸው የሱዳኑ ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በደቡብ አፍሪካ በሚገቡበት ጊዜ ሀገሪቱ ፕሬዚዳንቱን አሳልፌ አልሰጥም በማለቷ ነው ፍርድ ቤት የምትቀርበው። ፕሬዚዳንት አልበሽር ከሁለት ዓለም በፊት በደቡብ አፍሪካ በተካሄደው የአፍሪካ ህብረት ጉባዔ ላይ ለመካፈል በሄዱበት ጊዜ ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንቱን በቁጥጥር ስር እንድታውል ተጠይቃ እምቢ ማለቷ ይታወሳል። ደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንቱን በቁጥጥር ስር በማዋል ለፍርድ…

Read More

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች

ጣሊያን ለኢትዮጵያ የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች

ጣሊያን ለኢትዮጵያ ለግል ዘርፍ ልማት የሚውል የ500 ሺህ ዩሮ ድጋፍ አደረገች። ድጋፉ በዓለም ባንክ የዓለም ዓቀፉ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን የልማት መርሃ ግብሮች መካከል አንዱ ለሆነው “ለግል ዘርፉ ልማት መርሃ ግብር” ማስፈጸሚያ የሚውል ነው። ድጋፉ የተደረገው ከተለያዩ ለጋሽ አካላት ገንዘብ በማሰባሰብ ለታዳጊ አገሮች የግል ዘርፍ ድጋፍ በሚሰጠው “በመልቲ ዶነር ኢንሸቲቭ ፎር ፕራቬት ሴክተር ደቨሎፕመንት” በተሰኘው የጋራ ትብብር ማዕቀፍ በኩል ነው። የድጋፍ ስምምነቱ ፊርማ ስነ ስርዓትም ከሶስቱም ወገን ተወካዮች በተገኙበት በጣሊያን ኤምባሲ ዛሬ ተካሂዷል። ስምምነቱ ለግል ዘርፉ እድገት…

Read More

ከልዩ ቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ 40 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

ከልዩ ቦንድ ሽያጭ ሳምንቱ 40 ነጥብ 2 ሚሊየን ብር ተሰበሰበ

ከየካቲት 20 እስከ 29 በተካሄደው የልዩ ቦንድ ሽያጭ ሳምንት 40 ሚሊየን 212 ሺህ ብር መሰብሰቡን የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት አስታወቀ። በሳምንቱ ከቦንድ ሽያጩ በተጨማሪ ከልገሳ 948 ሺህ ብር ተገኝቷል። በልዩ ቦንድ ሸያጭ ሳምንቱ የተፈጠረው የህዝብ ንቅናቄ ከተጠበቀው በላይ እንደነበር የገለፀው ፅህፈት ቤቱ፥ ሽያጩ ከ50 ብር ጀምሮ የተካሄደ በመሆኑ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያሳተፈ እንደነበር አመላክቷል። ቢንሻንጉል ጉምዝ፣ አፋር፣ ጋምቤላ እና የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልሎች የቦንድ ሽያጩን ዘግይተው በመጀመራቸው ቀኑን አራዝመውታል። በአማራ፣ ደቡብ፣ ትግራይ እና…

Read More

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ከመጋቢት 4 ጀምሮ ይካሄዳል

የአማራ ክልል ምክር ቤት ጉባኤ ከመጋቢት 4 ጀምሮ ይካሄዳል

የአማራ ክልል ምክር ቤት ስድስተኛ መደበኛ ጉባኤውን ከመጋቢት 4 2009 ጀምሮ በባህርዳር ከተማ እንደሚያካሂድ አስታወቀ። የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ አቶ ይርሳው ታምሬ አንደገለጹት፥ ጉባኤው በክልሉ አስፈጻሚ አካላት የስድስት ወራት እቅድ ክንውንና በሌሎችም ጉዳዮች ላይ ይመክራል። በተጨማሪም በጥልቅ ተሃድሶው ማግስት የመጡ ለውጦችን በመገምገም የተለያዩ ውሳኔዎችን እንደሚያሳልፍና ሹመቶችንም እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል። የምክር ቤቱ ጉባኤ ከመጋቢት 4 2009 ዓ.ም ጀምሮ ለአራት ቀናት የሚካሄድ መሆኑን አፈጉባኤው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Read More

በደመወዝ ጭማሪው ባልተገባ መንገድ ለማትረፍ በሚሞክሩ ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

በደመወዝ ጭማሪው ባልተገባ መንገድ ለማትረፍ በሚሞክሩ ላይ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ተገለጸ

ለመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ጭማሪ በመደረጉ ሳቢያ በአንዳንድ የምግብ ሸቀጦችና የኢንዱስትሪ ምርቶች ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ነጋዴዎች ላይ ዕርምጃ መወሰዱን፣ ከዚህ በኋላም ዕርምጃ እንደሚወስድ ንግድ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ በቅርቡ በአዲስ አበባና በክልል ከተሞች በተደረገ የዳሰሳ ጥናት ያልተገባ የዋጋ ጭማሪዎች መታየታቸውን፣ የንግድ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ አሰድ ዚያድ ማክሰኞ የካቲት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ገልጸዋል፡፡ ከደመወዝ ጭማሪው ጋር ተያይዞ ሊከሰት የሚችለውን ክፍተት በመገመት ንግድ ሚኒስቴር ቀድሞ አንድ ኮማንድ ፖስት በማቋቋም ሲሠራ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡ በኮማንድ ፖስቱ…

Read More

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ምርጫና ጠቅላላ ጉባዔ አገደ

ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤትን ምርጫና ጠቅላላ ጉባዔ አገደ

የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ጠቅላላ ጉባዔ እንዳይካሄድ እንቅፋት ነበሩ ከተባሉ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤቶች መካከል አንዱ የሆነው፣ የአገር አቀፉ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ያካሄደው ጠቅላላ ጉባዔና የአመራሮች ምርጫ ተሰርዞ አዲስ ምርጫ እንዲካሄድ ተወሰነ፡፡ የዘርፍ ምክር ቤቱ ጠቅላላ ጉባዔና ምርጫ እንዲታገድና አዲስ ምርጫና ጠቅላላ ጉባዔ እንዲካሄድ የተወሰነው፣ የዘርፍ ምክር ቤቶችን ጉዳይ በቀጥታ ከሚመለከተውና ጉዳዩን ሲያጣራ በቆየው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ነው፡፡ ሰኞ የካቲት 27 ቀን 2009 ዓ.ም. ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የተጻፈው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው፣ አገር አቀፉ የኢትዮጵያ…

Read More
1 2 3