ከአዲስ አበባ ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የፊታችን እሁድ ሊጀመር ነው

ከአዲስ አበባ ካርቱም የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የፊታችን እሁድ ሊጀመር ነው

በአዲስ አበባና በካርቱም ከተሞች መካከል የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱን ለማስጀመር የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መደረሱን የኢፌዲሪ ፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ገልጿል፡፡ በሕዝብ ማመላለሻ አውቶብሶች የሚደረገው ድንበር ተሻጋሪ የሆነው  የአዲስ አበባ – ካርቱም የትራንስፖርት አገልግሎት አሁን ለደረሰበት ደረጃ የበቃው ከ8 ዓመታት ውጣ ወረድ መሆኑን በፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን የህዝብ አገልግሎትና ብቃት ማረጋገጫ ዳይሬክተሩ አቶ ተስፋዬ በላቸውበተለይ  ለኢቢሲ ተናግረዋል፡፡ ከባለሥልጣኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው፣ የመጀመርያው የአውቶብስ ትራንስፖርት አገልግሎት መጋቢት 3 ቀን 2009 ዓ.ም በይፋ ይጀመራል፡፡ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቱ በሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን…

Read More

በአንዋር መስጂድ ቦምብ በመወርወር ጉዳት አድርሷል የተባለው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

በአንዋር መስጂድ ቦምብ በመወርወር ጉዳት አድርሷል የተባለው ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት

በ2008 ዓመተ ምህረት ታህሳስ ወር በአዲስ አበባ ታላቁ አንዋር መስጂድ ቦምብ በመወርወር በ24 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል በተባለው ተጠርጣሪ ላይ ክስ ተመሰረተ። ተከሳሹ አህመድ ሙስጠፋ አብዶሽ የሚባል ሲሆን የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ኤረር ጓታ ነዋሪ ነው። ተከሳሹ በኢፌዲሪ ህገመንግስት የተረጋገጠውን የሃይማኖት ነጻነት በመቃረን ከራሳቸው አስተሳሰብ እና አስተምሮት ውጪ እምነትና አስተምሮ መኖር የለበትም የሚል አላማ በመከተል፤ በ2007 ዓ.ም በማህበራዊ ድረ ገጽ ከተዋወቀውና ካልተያዘ ግብረአበሩ ሼህ አሊ ሃይደር ጋር “አልሃበሽን እንናጥፋ” በሚል በኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል በኤረር…

Read More

3 ሺህ 400 የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአነስተኛ ኪራይ እንዲተላለፉ ተወሰነ

3 ሺህ 400 የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በአነስተኛ ኪራይ እንዲተላለፉ ተወሰነ

ግንባታቸው ተጠናቆ እጣ ያልወጣባቸው 3 ሺህ 400 የ10/90 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው ዜጎች በአነስተኛ ኪራይ እንዲተላለፉ ተወሰነ።በቅርቡም በካቢኔው ፀድቆ ወደ ተግባር ይገባል ተብሏል። የአዲስ አበባ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ እንዳለው፥ እጣ ወጥቶባቸው ርክክብ ያልተፈፀመባቸው ሌሎች 3 ሺህ 200 ቤቶችንም ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የሚያስችሉ ቅድመ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። የቢሮ ሀላፊ አቶ ይድነቃቸው ዋለልኝ ከፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ ቢሮው በቂሊንጦ ሳይት በአንድ አከባቢ የሚገኙትን ቤቶች ዝቅተኛ ገቢ ላላቸውና ለመንግስት ሰራተኞች በአነስተኛ ዋጋ ለማከራየት ከውሳኔ…

Read More

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞችን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፉ

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስደተኞችን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፉ

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዚዳንታዊ ስልጣናቸውን ተጠቅመው ስደተኞችን የተመለከተ አዲስ ውሳኔ አሳለፉ። አዲሱ ስደተኞችን የተመለከተ ውሳኔ የስድስት ሀገራት ዜጎች ለ90 ቀናት አሜሪካ እንዳይገቡ የሚከለክል ነው። ኢራቅ ከዚህ ቀደም በፕሬዚዳንቱ ወደ አሜሪካ እንዳይገቡ እገዳ ተጥሎባቸው ከነበሩ ሀገራት ውስጥ ወጥታለች። ህጋዊ ቪዛ የያዙ ኢራቃውያን አሜሪካ እንዲገቡ ይፈቀድላቸዋል። የጉዞ ትርምስን ለመቀነስም ከማርች 16 ጀምሮ ለ120 ቀናት ማንኛውም ስደተኛ አሜሪካ እንዳይገባ ተከልክሏል በአዲሱ ውሳኔ። የኢራን፣ ሊቢያ፣ ሶሪያ፣ ሶማሊያ፣ ሱዳን እና የመን ዜጎች በ90 ቀናት ውስጥ አሜሪካ እንዳይገቡ የጉዞ እገዳ…

Read More

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ

የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ጀመረ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሃድሶ ንቅናቄ የደረሰበት ሁኔታ እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዘመን አፈፃፀም ሪፖርት መገምገም ጀመረ። የኢህአዴግ ምክር ቤት ጽሕፈት ቤት በመግለጫው እንዳስታወቀው፤ ኮሚቴው ሪፖርቱን ከገመገመ በኋላ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ጀምሯል። ኮሚቴው ኢህአዴግ በይፋ የጀመረውን በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ከአመራር አባላቱና ከአባሉ አልፎ ወደ ሲቪል ሠራተኛውና ህዝቡ እንዲወርድ የተቀመጠው አቅጣጫ የታሰበለትን ዓላማና ግብ በትክክል ማሳካት አለማሳካቱን በዝርዝር ይገመግማል። በመግለጫው እንደተጠቀሰው፤ የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብና ተግባር ወኪል የሆኑት…

Read More

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ

 የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛ ስብሰባውን ማካሄድ ጀምሯል። የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ዛሬ የጀመረው ስብሰባ የጥልቅ ተሃድሶ ንቅናቄው የደረሰበት ሁኔታ እና የሁለተኛው የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዘመን ሁለተኛ ዓመት የግማሽ አመት አፈፃፀም ሪፖርትን በዝርዝር በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣል። ግምገማው ጥልቀትና ስፋት ይኖረው ዘንድ በቂ ዝግጅት መደረጉም ተገልጿል። የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ኢህአዴግ በይፋ የጀመረው እንደገና በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ ከአመራሩና ከአባሉ አልፎ ወደ ሲቪል ሰርቫንቱና ህዝቡ እንዲወርድ የተቀመጠው አቅጣጫ የታሰበለትን ዓላማና ግብ በትክክል ማሳካት አለማሳካቱን…

Read More

በቻይና ፓርላማ 100 ቢሊየነር አባላት ይገኛሉ

በቻይና ፓርላማ 100 ቢሊየነር አባላት ይገኛሉ

የቻይና ፓርላማ 100 ቢሊየነር አባላት እንዳሉት አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡ በቻይና ዓመታዊ የህግ አውጪወች እና አማካሪዎች ስብሰባ በቤጅንግ በተከፈተበት ወቅት አንድ ሪፖርት ከፖላንድ ወይም ከስዊድን ዓመታዊ ምርት እኩል ሃብት ያላቸው 100 ቢሊየነሮች በቻይና ፓርላማ ውስጥ አባል መሆናቸውን ይፋ አድርጓል፡፡ ቻይና የላይኛው እና የታችኛው በሚባሉ ምክር ቤቶቿ 5 ሺህ 129 ኣባላት አሏት፡፡ በሻንጋይ መሰረቱን ያደረገው ሑሩን የተሰኘ ሪፖርት 209 ያህሉ አባላት 507 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር አላቸው ሲል ይፋ አድርጓል፡፡ ሺ ጂን ፒንግ ወደ ስልጣን ከመጡበት የፈረንጆች 2013…

Read More

ሰሜን ኮሪያ አራት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

ሰሜን ኮሪያ አራት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን አስወነጨፈች

ሰሜን ኮሪያ አራት የባለስቲክ ሚሳኤሎችን ወደ ጃፓን አቅጣጫ ማስወንጨፏ ተነገረ።የደቡብ ኮሪያ ወታደራዊ ምንጮች እንደገለፁት፥ ሰሜን ኮሪያ ከቻይና ጋር ከምትዋሰንበት አከባቢ የተወነጨፉት ሚሳኤሎች 1 ሺህ ኪሎ ሜትር ከተጓዙ በኋላ “የጃፓን የኢኮኖሚ ዞን” ተብሎ በተከለለ አከባቢ ላይ ወድቀዋል።ባለፈው አርብ ሰሜን ኮሪያ በዩናይትድ ስቴትስ እና ደቡብ ኮሪያ እየተደረገ ላለው ወታደራዊ ልምምድ አፀፋ የሚሆን ሚሳኤል እንደምትተኩስ አስጠንቅቃ ነበር።ዛሬ ማለዳ ላይ የተተኮሱት ሚሳኤሎች ዓይነት በዝርዝር አለመታወቁ ነው የተገለፀው።ሆኖም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰሜን ኮሪያ ምንም ዓይነት ሚሳኤልም ሆነ የኑክሌር ሙከራ እንዳታደርግ…

Read More

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ማጭበርበር በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ታጣለች

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ማጭበርበር በየዓመቱ ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ታጣለች

ኢትዮጵያ በቴሌኮም ዘርፍ በሚፈጸም ማጭበርበር ምክንያት በየዓመቱ ማግኘት የሚገባትን ከ1 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ እንደምታጣ ተነገረ። ኢትዮ ቴሌኮም ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለጸው፥ የቴሌኮም ማጭበርበርን ለመቆጣጠር በቴክኖሎጂ የታገዘ የመከላከል ስራዎች እየተከናወኑ ነው። የኩባንያው የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱራሂም አህመድ፥ መልኩን እየቀያየረ የመጣው የቴሌኮም ማጭበርበር ተግባር ከመደበኛ ስልክ ወደ ተንቀሳቃሽ ስልኮች ትኩረቱን እንዳደረገ ተናግረዋል። የወንጀል ድርጊቱ በሃገራዊ ደህንነት ላይ የሚያሳድረው ተፅእኖ ቀላል እንዳልሆነ የገለጹት አቶ አብዱራሂም፥ በእንዲህ መልኩ ገቢዉን የሚያገኙ አካላትም በአብዛኛው ለሽብር ድርጊት የሚያውሉ…

Read More

ሽብር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በምዕራብ ትግራይ ዞን የተያዙ 76 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

ሽብር ለመፈፀም ሲንቀሳቀሱ በምዕራብ ትግራይ ዞን የተያዙ 76 ግለሰቦች ፍርድ ቤት ቀረቡ

በኤርትራ ከአሸባሪው ግንቦት ሰባት የሽብር ተልእኮ ወስደው በሀገር ውስጥ ሽብር ለመፈጸም በምዕራብ ትግራይ ዞን ቃፍታ ሁመራ ወረዳ የተያዙ 76 ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።ግለሰቦቹ ቃፍታ ሁመራ ላይ በፀጥታ ሃይሎች ላይ ተኩስ በመክፈት የሁለት የጸጥታ አስከባሪዎች ህይወት እንዲያልፍ ማድረጋቸው በቀረበባቸው ክስ ላይ ተጠቅሷል ።ዛሬ የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 19ኛ ወንጀል ችሎት ለቀረቡት ተከሳሾች የክስ ሰነዱ እንዲደርሳቸው ያደረገ ሲሆን፥ ክሱን ለማንበብም ለረቡዕ የካቲት 29 ቀን 2009 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።1ኛ ሚፍታህ ሼክሱሩር፣ 2ኛ ግርማ ፈቀደ፣ 3ኛ እሸቴ…

Read More
1 2