በሀሰተኛ ምስክሮች ፍትህ እንዳይዘባ የሀይማኖት አባቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

በሀሰተኛ ምስክሮች ፍትህ እንዳይዘባ የሀይማኖት አባቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ

መቀሌ  የካቲት 26/2009 በሀሰተኛ ምስክሮች  ፍትህ እንዲዘባ የሚደረጉ ሙከራዎችን ለመግታት  የሀይማኖት አባቶች የድርሻቸውን እንዲወጡ ተጠየቀ፡፡ የትግራይ ክልል ፍትህ ቢሮ  በህግ ስርፀት፣ የእውነተኛ ምስክርነት አሰጣጥ፣የጠበቆችና ወሳኝ ኩነት ምዝገባ   ሚዛናዊነት ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ከህዝብ ክንፍ አደረጃጀቶችጋር በአክሱም ከተማ ተወያይቷል፡፡ በቢሮው  የወንጀል ጉዳይ አስተባባሪ አቶ ጎይቶኦም ገብረማርያም በውይይቱ ላይ እንዳሉት በሀሰተኛ ምስክሮች በክልሉ  ፍትህን ለማዛበት  የሚደረጉ ሙከራዎች አሉ፡፡ በገንዘብና በሌሎችም መደለያዎች ሀሰተኛ ምስክር የሚሆኑ ግለሰቦች ቁጥር እየተበራከተ መምጣቱን ጠቁመው  በተጨማሪም  የሚያውቁት ነገር በትክክል አለመናገርና እንደማያውቁ መምሰል ሌላው ችግር…

Read More

ሜርክል በሰሜን አፍሪካ ጉብኝታቸው በስደተኞች ዙሪያ መክረዋል

ሜርክል በሰሜን አፍሪካ ጉብኝታቸው በስደተኞች ዙሪያ መክረዋል

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል የሰሜን አፍሪካ ሃገራትን ሲጎበኙ ህገወጥ ስደተኞችን መከላከል በሚቻልበት ዙሪያ ከሃገራቱ ጋር መክረዋል፡፡ መራሂተ መንግስቷ ባለፈው ሳምንት ወደ ግብፅና ቱኒዚያ ያቀኑበት ዋናው  ምክንያት ሁለት ሚሊዮን ስደተኞች በሀገራቸው ጀርመን እንዲጠለሉ መፍቀዳቸውን ተከትሎ ጫናው እየከበደ በመምጣቱ ነው፡፡ በካይሮ ዩኒቨርሲቲ የዓለም  አቀፍ ግንኙነት ፕሮፌሰር ታሪቅ ፋህማይ እንደገለጹት ስደተኞች በሜዲትራኒያን ባህር  ወደ አውሮፓ ለማቋረጥ በዋናነት ግብፅና ቱኒዚያ ይጠቀማሉ፡፡ ዢንዋ  እንደዘገበው ከሆነ የሜርክል ግብፅና ቱኒዚያ ጉብኝት ወደ  ጀርመንና አውሮፓ የሚገቡትን ስደተኞች ቁጥር ለመቀነስ  ነው፡፡ ሜርኬል የፖለቲካ ዓለመረጋጋት የሚታይባትንና የሁለቱ ሀገራት ጎረቤት የሆነችውን ሊቢያንም ጎብኝተዋል፡፡ በሃገሪቱ ያለውን የፖለቲካ አለመረጋጋትን ተጠቅመው ህገወጥ የሰዎች ዝውውርን ለሚያባብሱትም መፍትሄ በሚበጅለት ዙሪያ መምከራቸውን ዘገባው አመልክቷል፡፡ ሊቢያ…

Read More

አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት- ጠ/ሚ ኃይለማርያም

“አፍሪካውያን ችግሮቻቸውን በራሳቸው ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል ይኖርበታል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ ገለጹ። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም በኡጋንዳ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ከፕሬዚዳንት ዮዌሪ ካጉታ ሙሴቬኒ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል። ከሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ ግንኙነት ባሻገር አካባቢያዊና አህጉራዊ ጉዳዮችም በመሪዎቹ ውይይት ተዳሷዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ከውይይቱ በኋላ እንደገለጹት፥ በሶማሊያ ሰላም ለማስፈን የተደረገው ጥረት ውጤት አስመዝግቧልያሉ ሲሆን፥ ለዚህም በጥምረት የተደረገውን ጥረት አድንቀው፤ ኡጋንዳም ለከፈለችው መስዋዕትነት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። “ለሶማሊያ ሰላምና መረጋጋት የተሰራው ስራ እና የተገኘው ውጤት አፍሪካ…

Read More

‹‹መታገል ያለብን ራሱን ለመጥቀም የሚሠራውን አመራር ነው››

‹‹መታገል ያለብን ራሱን ለመጥቀም የሚሠራውን አመራር ነው››

አቶ ዘነበ ኩሞ፣ የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራ ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ቀድሞ የፌዴራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኤጀንሲ ተብሎ ይጠራ የነበረው መሥሪያ ቤት በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ ቁጥር 372/2008 ሁለት ቦታ ተከፍሏል፡፡ ተጠሪነቱ ለከተማ ልማት ሚኒስቴር የሆነው የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲም በደንብ ቁጥር 374/2008 ተቋቁሟል፡፡ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ ልማት ማኑፋክቸሪንግ ኤጀንሲ ሁለተኛው ሲሆን፣ ተጠሪነቱ ለንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ አቶ ዘነበ ኩሞ የፌዴራል ከተሞች ሥራ ዕድል ፈጠራና ምግብ ዋስትና ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ናቸው፡፡…

Read More

ከረሃብና ከድርቅ ለምን መውጣት አቃተን?

ከረሃብና ከድርቅ ለምን መውጣት አቃተን?

ምቹ ተፈጥሮ እያላት ምግብ የሚታደልባት አገር ኢትዮጵያ ብቻ ናት · ቦትስዋና 90 በመቶ መሬቷ በረሃማ ነው፤ ግን ራሳቸውን ይቀልባሉ · ደቡብ አፍሪካ በድርቅ ተጠቂ ብትሆንም የተትረፈረፈ ምርት አምራች ናት ዶ/ር ቆስጠንጢኖስ በርሄ (የምጣኔ ሃብት ምሁር) ለምንድን ነው ድርቅ የሚያስከትለውን አደጋ መከላከል ያቃተን? በመጀመሪያ ደረጃ መታየት ያለበት ሀገሪቱ ምን አይነት አቅም አላት የሚለው ነው፡፡ ኢትዮጵያ 70 ሚሊዮን ሄክታር የሚታረስ መሬት አላት ያለው ራሱ የግብርና ሚኒስቴር ነው፡፡ ከዚህ ውስጥ ቢበዛ 14 በመቶውን ነው እየተጠቀምን ያለነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ፤…

Read More

ቻይና የ2017 አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት እቅዷን ቀነሰች

ቻይና የ2017 አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት እቅዷን ቀነሰች

ቻይና እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ2017 አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት እቅድ ወደ 6 ነጥብ 5 ዝቅ መደረጉን የሀገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ አስታወቁ።ሀገሪቱ በተያዘው ዓመት 6 ነጥብ 5 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ለማስመዝገብ ያቀደች ሲሆን፥ አምና በተመሳሳይ ካስቀመጠችው ከ6 ነጥብ 5 እስከ 7 በመቶ የቀነሰ ነው ተብሏል።የቻይናው ጠቅላይ ሚኒስትር ሊኪ ኪያንግ ዛሬ በሀገሪቱ ፓርላማ ቀርበው የሀገሪቱን የስራ ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት ነው ይህን ያስታወቁት።ቻይና በፈረንጆቹ 2016 6 ነጥብ 7 በመቶ አጠቃላይ ሀገራዊ እድገት ያስመዘገበች ሲሆን፥ ከፍተኛ የባንክ ብድር…

Read More

በምስራቅ ሸዋ ዞን 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተያዙ

በምስራቅ ሸዋ ዞን 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶች ተያዙ

በምስራቅ ሸዋ ዞን ቦራ ወረዳ 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ከትክክለኛ የብር ኖቶች ጋር ቀላቅሎ ሲገበያይ የነበረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር መዋሉን ፖሊስ አስታወቀ።የምስራቅ ሸዋ ዞን ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ባልደረባ ምክትል ኮማንደር አስቻለው ዓለሙ እንደገለጹት ግለሰቡ ትናንት የተያዘው በሳምንት አንድ ቀን በሚውለው የአለም ጤና ከተማ ገበያ ላይ ነው።ግለሰቡ በቁጥጥር ስር ሊውል የቻለው 4 ሺህ 300 ሀሰተኛ የብር ኖቶችን ከትክክለኛው የብር ኖቶች ጋር በመቀላቀል ብዙ ኩንታል ጤፍ እየሸመተ በነበረበት ወቅት ሕብረተሰቡ ለፖሊስ ባደረሰው ጥቆማ ነው።ግለሰቡ በወቅቱ…

Read More

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስተጓጎልና ነዳጅ እንዳዳይገባ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ተከሰሱ

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማስተጓጎልና ነዳጅ እንዳዳይገባ ለማድረግ ተንቀሳቅሰዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ተከሰሱ

በክሱ 12 ኤርትራውያን ተካተዋል የሚኒስትሮች ምክር ቤት መስከረም 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ እንዳይሆንና ነዳጅ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ለማድረግ፣ በኤርትራ ሥልጠና ወስደው ወደ ኢትዮጵያ በመግባት በመንቀሳቀስ ላይ እያሉ በቁጥጥር ሥር ውለዋል የተባሉ 77 ግለሰቦች ክስ ተመሠረተባቸው፡፡ ሁሉም ተከሳሾች ከጥር 2 ቀን 2007 ዓ.ም. ጀምሮ ውህደት በመፍጠር ‹‹አርበኞች ግንቦት ሰባት ለአንድነትና ለዴሞክራሲ›› እየተባለ ለሚጠራው ድርጅት አባል በመሆን፣ ዓላማውንና ተልዕኮውን ለመፈጸም ወታደራዊና ፖለቲካዊ ሥልጠና ወስደው የአገሪቱን ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ተቋማትን ለማናጋት ሲንቀሳቀሱ…

Read More

የትራፊክ ሥርዓት የማታውቀው ከተማ

የትራፊክ ሥርዓት የማታውቀው ከተማ

ጠመዝማዛውን መንገድ ጨርሰው የዳዬ ከተማ መግቢያ ላይ ብቅ ሲሉ በርካታ የሞተር ሳይክሎች ይመለከታሉ፡፡ አልፎ አልፎም ባለ ሦስት እግር ባጃጆች ይታያሉ፡፡ ሞተር ሳይክሎቹ ግን ለከተማው ነዋሪዎች ብቸኛ የትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ናቸው፡፡  መንገዱ ላይ የተኮለኮሉት ሞተረኞች ደንበኛ የተገኘ ሲመስላቸው ተሳፋሪውን ለመውሰድ ይሻማሉ፡፡ ቀልጣፋው የመጣውን ደንበኛ እንደወሰደ ሁሉም ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ፡፡ ተራ ጠብቆ መሥራት የሚባል ነገር ያለ አይመስልም፡፡ ይህ ብቻም አይደል በአንድ ሞተር ላይም እስከ ስድስት ተሳፋሪዎችን መጫን የተለመደ ነው፡፡ ጫት፣ ጣውላ፣ ቆርቆሮና ሌሎች ነገሮችም የሚያስጭን ደንበኛ ከተገኘም…

Read More
1 2