ደቡብ ኮሪያ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገች

ደቡብ ኮሪያ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ አደረገች

የደቡብ ኮሪያ መንግስት በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች የሚውል የ500 ሺህ ዶላር ድጋፍ ማድረጉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ገለጸ።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ኪም ሙን ሀን የገንዘብ ድጋፉን ለኮሚሽኑ አስረክበዋል።

አምባሳደር ቲም ሙን ሀን እንደተናገሩት፤ ደቡብ ኮሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ባላት የቆየ ወዳጅነትና ትብብር የቅርብ ድጋፍ ማድረጓን ትቀጥላለች።

ድጋፉ በጥር 2016 የወጣውን የሰብዓዊ ሰነድ መነሻ በማድረግ በድርቁ ለተጎዱ ወገኖች እንዲውል የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

የኮሚሽኑ የቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ዳይሬክተር አቶ ሙሉነህ ወልደማርያም እንደገለጹት፤ ድጋፉ ድርቁ በተከሰተባቸው የተለያዩ አካባቢዎች ለሚገኙ ተጎጂዎች ይውላል።

በኢትዮጵያ በ2007/2008 ዓ.ም በኤልኒኖ ክስተት የመኸርና የበልግ ዝናብ እጥረት በተከሰተው ድርቅ 10 ነጥብ 2 ሚሊዮን ህዝብ ለጉዳት መጋለጡ ይታወሳል።

ምንጭ፦ ኢዜአ

Leave a Comment