አንድ የኤርትራ አየር ሀይል አብራሪ የውጊያ ጄቱን ይዞ በዛሬው እለት ኢትዮጵያ ገባ።

ሰበር ዜና

ዛሬ ጥዋት 4 ሰዓት ላይ የኢሳያስ መንግስት አየር ሃይል MIG 29 የጦር ኣውሮፕላን ኣብራሪ የሆኑት መቶ ኣለቃ መብራሃቱ ተስፋማሪያምና አፈወርቅ ፀሃየ የተባሉ ሁለት ካፕቴኖች የክንፍ ቁጥሩ 102 የሆነውን zlin 143 ኣውሮፕላን ይዘው መቀለ በማረፍ እጃቸውን ለኢትዮጵያ መንግስት መስጠታቸው ታውቋል ። ዛሬ ከጠዋቱ 3 ሰዓት ከኣስመራ የተነሳውና ስሪቱ የቼክ ሪፐብሊክ የሆነው zlin 143 ኣውሮፕላን ዋናው ተግባሩ የቅኝት ስራና የመለማመጃ እንደሆነ ታውቋል። እንደ የኢትዮጵያ አየር ሃይል ምንጮች ከሆነ ኣውሮፕላኑ የኢትዮጵያ የአየር ክልልን አልፎ ከመግባቱ በፊት ኣብራሪዎቹ በአውሮፕላኑ ውስጥ ምንም ነገር አለመያዛቸውንና አደጋ የማድረስ ሃሳብ እንደሌላቸው አስታውቀው እጃቸውን ለመስጠት መምጣታቸውን በመግለፅ እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ጠይቀው መቀለ ለማረፍ ማስፈቀዳቸው ተገልፅዋል ። የኢትዮጵያ አየር ሃይል ይበልጥ እርግጠኛ ለመሆን እጃቸውን የሰጡት ኣብራርዎች በእርግጥ አደጋ እንደማያደርሱና ምናልባትም ሌሎች አደጋ ለማድረስ ተከትለዋቸው የሚመጡ አውሮፕላኖች እንዳይነሩ በሚል SU 27 የጦር ጀቶች እንዲነሱ በማድረግ አውሮፕላኑ የኢትዮጵያ አየር ክልል ሲደርስ አጅበው መቀለ እንድያርፍ እንዳደረጉት ከኢትዮጵያ አየር ሃይል ከተገኘው መግለጫ ለማወቅ ተችሏል ።

Leave a Comment