በደቡብ ሱዳን የመንገደኞች አውሮፕላን ተከሰከሰ

የመንገደኞች አውሮፕላን በደቡብ ሱዳን ዋኡ አውሮፕላን ማረፊያ መከስከሱ ተሰምቷል።አውሮፕላኑ 44 መንገደኞችን አሳፍሮ እንደነበር የተነገረ ሲሆን፥ በአደጋው አብዛኞቹ ተሳፋሪዎች ሳይሞቱ አይቀርም ተብሏል።የሀገሪቱ የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ቦና ጋውዴንሲዮ እስካሁን ባለው ሁኔታ 14 ተሳፋሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል ማለታቸውን ሜትሮ ዘግቧል።

በጁባ የሚገኝ አይ የተሰኘ የሬዲዮ ጣቢያ አንድ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ዘጠኝ ሰዎች በህይወት ተርፈው ወደ ሆስፒታል ተወስደዋል።ለሬውተርስ አስተያየት የሰጡ የአደጋ ጊዜ ሰራተኛ ግን “አንድም የአውሮፕላኑ ተሳፋሪ አልሞተም፤ በርካቶቹ ግን ጉዳት ደርሶባቸዋል” ብለዋል።አውሮፕላኑ ከጁባ መነሳቱ እና በዋኡ አውሮፕላን ማረፊያ ሊያርፍ ሲሞክር የመከስከስ አደጋው ሳያጋጥመው እንዳልቀረ ነው የተነገረው።ሀገሪቱ ባለስልጣናትም አደጋውን አስመልክቶ የሚሰጡት መግለጫ እየተጠበቀ ነው።

Leave a Comment