በአዲስ አበባ ባለፈው ነሐሴ በከባድ ሌብነት ወንጀል የተጠረጠሩ 187 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር ውለዋል

በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ነሐሴ ወር በከባድ ሌብነትና ዝርፊያ ወንጀል 187 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ፡፡

በኮሚሽኑ የከባድ ሌብነትና ዝርፊያ ወንጀል ምርመራ ኃላፊ ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ተጠርጣሪዎቹ በከተማዋ አሥሩም ክፍለ ከተሞች በቅሚያ፣ የመኪና ዕቃ ስርቆት፣ አደገኛ ዕፅ ማዘዋወርና ሌሎች የወንጀል ድርጊቶች የተጠረጠሩ እንደሆኑም አስታውቀዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹን በቁጥጥር ሥር በማዋል ሂደት ውስጥ የሕብረተሰቡ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደሆነም ኮማንደር አለማየሁ ተናግረዋል፡፡

በቀጣይም ኮሚሽኑ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ ሕብረተሰቡ ተሳትፎውን አጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ዘገባው ሙባረክ ሙሀመድ ነው፡፡

Leave a Comment