ሶማሊያውያኑ ሙሽሮች የሰርጋቸውን ወጪ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለገሱ

ሶማሊያውያኑ ጥንዶች የሰርጋቸውን ወጪ በድርቅ ለተጎዱ ወገኖች ለግሰዋል፡፡ ከጋልካሲዮ አካባቢ የተገኙት እነኝህ ጥንዶች ሊባን እና አይሻ ይባላሉ፡፡ሙሽሮቹ ለመጋባት የቆረጡት ቀን ደርሶ ትዳር ሲመሰርቱ በሰርጉ ስም ለድግስ እና ለሌሎች ወጪዎች የታቀደውን ሁሉ ገንዘብ ማባከን ነው በሚል ለሌላ በጎ ዓላማ አቀዱት፡፡በዚህም ሳያበቁ ገንዘቡን ለድርቅ ተጎጂዎች የተለያየ ድጋፍ ማድረጋቸው ነው የተገለጸው፡፡

“የተባረከውን ጋብቻችንን ስንፈፅም የተራቡትንም በማሰብ ሊሆን ይገባል” በሚል ነው እርዳታውን ያደረጉት ተብሏል፡፡የሰርጉን ወጭ ለመሸፈን በተዘጋጀው ገንዘብ ለድርቅ ተጎጂ ሶማሊያውያን ውሃ፣ ምግብ እና የህክምና ቁሳቁስ ገዝተው አበርክተዋል፡፡

ሙሽሮቹ በበጎ ተግባራቸው አድናቆትን አግኝተዋል፡፡በማህበራዊ ድረገፆችም ትዳራችሁ ይባረክ፣ መጪ ዘመናችሁ በደግነት የተሞላ ይሁን የሚሉ መልካም ምኞቶች ተችሯቸዋል፡፡ ምንጭ፡-www.tuko.co.ke

 

 

Leave a Comment